News and events Detail


Blog Image

ባለሥልጣኑ በፍቼ ከተማ የአረንጓዴ አሻራና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተከናወነ

  • HEMIS System
  • 06-Aug-2022

ባለሥልጣኑ በፍቼ ከተማ የአረንጓዴ አሻራና  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተከናወነ

==>የ5 አቅመ-ደካሞች ቤት እድሳት ተከናውኗል፤

==>ለ250 ችግርተኛ ተማሪዎች የደብተር፣ የስክሪፕቶ እና የመማሪያ ቅሳቁስ መያዣ ቦርሳ ተበርክቷል፤

======= #WMCC=========

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮችና ሰራተኞች  በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በፍቼ ከተማ አስተዳደር አበበች ጎበና ተብሎ በሚጠራው የመታሰቢያ ቦታ በመገኘት “አረንጓዴ አሻራችን ለትውልዳችን!” በሚል መሪ-ቃል ችግኝ በመትከል የአረንጓዴ አሻራ እና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አከናውነዋል።

ከአረንጓዴ አሻራው መርሃ-ግብሩ በተጨማሪ ለአምስት አቅመ ድካሞችን ቤት እድሳት የሚውል ቆርቆሮ ገዝቶ ማቅረብን ጨምሮ የቤት እድሳቱን የማስጀመር ስራ ተከናውኗል፤ እንዲሁም   ለ250 ተማሪዎች ከ200 ሺ ብር በላይ የሚገመት የደብተር፣ የስክሪፕቶ፣እና የመማሪያ ቁሳቁስ መያዣ ቦርሳ የማበርከት ድጋፍ ተደርጓል።

በመርሃ-ግብሩ የባለሥልጣኑ አመራሮችና ሰራተኞች፣  የፍቼ ከተማ ከንቲባ አቶ ክፍሉ ከበደ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።

ሐምሌ 28 ቀን 2014 ዓ.ም