News and events Detail


Blog Image

በ2014 እቅድ አፈጻጸም፣ በ2015 በጀት ዓመት እቅድ እና በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት ተካሄደ

  • HEMIS System
  • 31-Jul-2022

የኢፌዲሪ ትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አመራሮች እና ሰራተኞች በ2014 እቅድ አፈጻጸም፣ በ2015 በጀት ዓመት እቅድ እና በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ፤ እንዲሁም ከአዲስ የምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ጋር የትውውቅ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ከተማ ቢን ኢንተርናሽናል ሆቴል ተካሄዱ። በመርሃ-ግብሩ መግቢያ ላይ በተደረገው የአዳዲስ አመራሮች ትውውቅ  ዶ/ር ዱንካና ኑጉሳ   የእውቅናና ስታንዳርዳይዜሽን ም/ዋና ዳይሬክተር፣ አቶ ውብሸት ታደሰ የፈቃድ አሰጣጥ  እና ጥራት ኦዲት ም/ዋና ዳይሬክተር ፣ አቶ ቸሩጌታ ገነነ  የኢንስፔክሽንና የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥና ቁጥጥር ም/ዋና ዳይሬክተር ከባለሥልጣኑ ማህበረሰብ ጋር እንዲተዋወቁ የተደረገ ሲሆን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ መድረኩን በንግግር ከፍተዋል።


የባለሥልጣኑ እቅድ ዝግጅትና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በቀለ ከተማ የ2014 እቅድ አፈጻጸም የትምህርት ጥራት ኦዲትና አቅም ማጎልበት፣ የእውቅና አሰጣጥ፣ የትምህርት ማረጋገጥና የአቻ ግምት፣ እንዲሁም በድጋፍ ሰጪ አገልግሎቶች የተከናወኑ ስራዎች ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም  99.19 በመቶ በማከናው የተሻለ ስራ ተከናውኗል ብለዋል። 

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የባለሥልጣኑ የበጀት አፈጻጸም 99.63 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል።


የባለሥልጣኑ የመፈጸም አቅም ማደግ፣ በውስን የሰው ሀይልና የግብዓት እጥረት አብቃቅቶ መጠቀም፣ ከወረቀት ወደ ዲጂታል አሰራር መቀየር፣ የክትትል ስራና የእርምት እርምጃን አጠናክሮ መቀጠል፤ የባለሥልጣን መዋቅር እንዲጸድቅ እየተደረገ ያለው፤ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 515/2014 ማጸደቅ እና በጀትን ለታቀደለት አላማ አሟጦ መጠቀም በ2014 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ናቸው።  በመቀጠልም የ2015 በጀት ዓመት የስራ እቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። ከሠራተኞች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በዋና ዳይሬክተር ዶክተር አንዱዓለም አድማሴ እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እንዲሁም በተለያዩ የስራ ክፍል ሃላፊዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡


ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም